Загрузка...

የአሜሪካ አማራጭ የጦርነት እቅዶች?! እስራኤል የከፈተችው የድሮን ፋብሪካ! | Israel Opened New Drone factory!

📌 ትኩስ እና ተዓማኒ ሰበር መረጃዎችን በፅሁፍ ለማንበብ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!
በቪዲዮው ከሰማችሁት በተጨማሪ ዝርዝር ዘገባዎችን፣ ሰነዶችን እና ወቅታዊ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በድረ-ገጻችን ላይ መጫን ጀምረናል። አሁኑኑ ሊንኩን በመንካት ትኩስ መረጃዎችን ያግኙ፡
👉 https://gebeyaethiopia.com
ገበያ ሚዲያ - ከዜና በላይ ጥልቅ ትንታኔ!

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ የአሜሪካ-እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉትን ጦርነት ለማቆም በሚያስችለው እምቅ ስምምነት ላይ እየተደረገ ባለው ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ዙሪያ "ጥቂት መሻሻሎች ታይተዋል፣ ይህም ጥሩ ነገር ነው" ብለዋል። ይሁን እንጂ ሩቢዮ በኢራን የኒውክሌር ማበልጸግ ሂደት ላይ ስላልተፈቱ ልዩነቶች ጥቅስ በማድረግ እና ኢራን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ "የክፍያ ስርዓት (tolling system) ለመዘርጋት" የምታደርገው ጥረት "ተቀባይነት የሌለው" መሆኑን በመግለጽ፣ ለሰላም ስምምነቱ የነበረውን ከፍተኛ ግምት ወይም ተስፋ ገታ አድርገውታል።
 
አክለውም ኢራን የባህር ሰርጡን በድጋሚ ለመክፈት ፈቃደኛ ካልሆነች አሜሪካ እና አጋሮቿ "ሌላ አማራጭ እቅድ (Plan B)" ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናግረዋል። ለመሆኑ ፕላን ቢው ምንድን ነው። በጦርነቱ ጋር በተያያዘ ምን አይነት አንድምታስ ይኖረዋል ?

አሜሪካ እስራኤልን ከኢራን ለመከላከል ስትል ‘ከመጥለፊያ ሚሳኤሎቿ መካከል ግማሹን ያህሉን ማጣቷ ተዘግቧል። ፈጣኑ የሚሳኤል ክምችት መመናመን አሜሪካ ሌሎች ወታደራዊ ስጋቶችን የመከላከል አቅሟ ላይ ስጋት እየፈጠረ መሆኑን የዘገበው ዋሽንግተን ፓስት ነው። አሜሪካ እስራኤልን ከኢራን ጥቃቶች ለመከላከል ስትል ካላት የፀረ-ባለስቲክ ሚሳኤል ክምችት ውስጥ ግማሹን ማሟጠጧ ተዘግቧል።

በተጨማሪም ኢራን የሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) ምርቷን እንደገና መጀመርን ጨምሮ ወታደራዊ አቅሟን ከሚጠበቀው በላይ በሆነ ፍጥነት መልሳ እየገነባች መሆኑን ሲኤንኤን (CNN) ዘግቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ የእስራኤል የዜና ማሰራጫ ቻናል እንደዘገበው በደርዘን የሚቆጠሩ የጭነት አውሮፕላኖች ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከጀርመን ከሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፖች ወደ እስራኤል ትላልቅ የጦር መሳሪያዎችን ማጓጓዛቸውን ዘግቧል፣ ይህም ዋሽንግተን እና ቴል አቪቭ በቴህራን ላይ አዲስ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው የሚል ግምትን አባብሷል። እስራኤል በሰርቢያ መንግስት ባለቤትነት የተያዘ የድሮን ፋብሪካ 51 በመቶ ድርሻ ይዛ ስራ ለመጀመር የተዘጋጀችው ባሰለፍነወ ሚያዚያ ወር መጨረሻ አከባቢ ነበር። እስከመጨረሻው አብራችሁን በመቆየት እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።
 
In a statement on Friday, U.S. Secretary of State Marco Rubio noted that "some progress has been made, which is a good thing" regarding the ongoing indirect negotiations on a potential agreement to end the U.S.-Israel war with Iran. However, Rubio tempered high expectations for a peace agreement by citing unresolved differences over Iran's nuclear enrichment process and declaring Iran's efforts to establish a "tolling system" in the Strait of Hormuz as "unacceptable."
He added that if Iran refuses to reopen the strait, the U.S. and its allies must have a "Plan B." What exactly is this Plan B? And what implications will it have regarding the war?
Meanwhile, it has been reported that the U.S. has lost nearly half of its interceptor missiles while defending Israel from Iran. According to The Washington Post, this rapid depletion of the missile stockpile is raising concerns about the U.S.'s ability to defend against other military threats. The report noted that the U.S. has exhausted about half of its anti-ballistic missile inventory to shield Israel from Iranian attacks.
Additionally, CNN reported that Iran is rebuilding its military capabilities at a faster-than-expected rate, which includes resuming its unmanned aerial vehicle (drone) production.
On the other hand, an Israeli news channel reported that dozens of cargo planes have transported large quantities of weapons from U.S. military bases in Germany to Israel over the past 24 hours. This has fueled speculation that Washington and Tel Aviv are preparing to take new military action against Tehran. It is worth noting that around the end of this past April, Israel was prepared to begin operations after acquiring a 51% stake in a Serbian government-owned drone factory. We invite you to stay with us until the very end to follow the details.
 
#GebeyaMedia #GebeyaPodcast #MiddleEastCrisis #USIranTension #IsraelIranWar #StraitOfHormuz #PlanB #MilitaryNews #MissileDefense #DroneTechnology #DefenseLogistics #WeaponStockpile #WashingtonPost #CNNReport

Видео የአሜሪካ አማራጭ የጦርነት እቅዶች?! እስራኤል የከፈተችው የድሮን ፋብሪካ! | Israel Opened New Drone factory! канала Gebeya Media - ገበያ
Яндекс.Метрика
Все заметки Новая заметка Страницу в заметки
Страницу в закладки Мои закладки
На информационно-развлекательном портале SALDA.WS применяются cookie-файлы. Нажимая кнопку Принять, вы подтверждаете свое согласие на их использование.
О CookiesНапомнить позжеПринять