Загрузка страницы

[በ2012 ዓ.ም ምድራችንን የሚገጥሟት ከባባድ ፈተናዎች] መገቢ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ!

ምድራችን በእኛ አቆጣጠር በ2012 ዓ.ም. በፈረንጆቹ 2020 ዓ.ም. ላይ በከባድ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈች ነው። እጅግ ጥንታዊው ከ1200 ዓመታት በፊት የነበረው የማያ የዘመን ቀመር ዐዲስ ያልተለመደ ክስተት የሚጀምርበት ዑደቱ የሚጠናቀቅበት የተፈጥሮ አደጋዎች በዝተው የሚታዩበት 2012 ላይ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ብዙ ዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎች በፈረንጆቹ 2012 ላይ መስሏቸው ብዙ አስተያየት በጊዜው ሲሰጡ ቆይተው ነበር። 2012 የሚል አስፈሪ ፊልም ከማያ የዘመን ቀመር በመነሣት የፈረንጆቹ 2012 ከመድረሱ 3 ዓመት ቀድሞ በ2009 ላይ በሆሊውድ ተሠርቶ በሮናልድ ኤመሪክ ዳይሬክት ተደርጎ ሁላችንም ተመልክተነዋል።

❤️ ነገር ግን በፈረንጆቹ 2012 ምንም ሳይከሠት የእኛው 2012 ዓ.ም ደርሷል። የእኛው 2012 ዓመት ግን ገና ከመጀመሩ ለዓለማችን አስደንጋጭ ሆኗል። በዚህ ዓመት ምድራችንን የገጠሟት በርካቶች ነገሮች ቢሆኑም ከነበሩት አስደንጋጭ ጉዳዮችና በዚህ ዓመት ከሚያጋጥሟት ዋና ዋናዎቹን ክስተቶች በጥቂቱ መርጬ እጽፋለሁ፦

1ኛው) ከፈረንጆቹ የልደተ ክርስቶስ በዓል አስቀድሞ እጅግ አውዳሚና አደገኛ 310442 (2000 CH59) የተባለው ግዙፍ አስቴሮይድ (ዐለት) ከፈረንጆቹ ገና (Christmas) በፊት ታኅሣሥ 16 (December 26) በእኛ 4:54 ወይም 2:54 a.m. EST ላይ ምድርን አልፏት መሄዱ ነበር ። ይህንንም ኢንዲፔንደንት "የገና ተአምር" በሚል አስነብቦ ነበር። ይህም ዐለት ቢወድቅ ኖሮ በኒውዮርክ የሚገኘው 1,792 ጫማ የሚሆነውን ትልቁን የመገበያያ ማዕከል (Trade Center) የሚበልጥ ነበርና ምድር ላይ ከባድ ጉዳት ያስከትል ከባድ ሱናሚ ያስከትል ነበር።

2ኛው) በ2012 ዓ.ም ላይ ከመስከረም ጀምሮ እስከ ጥር የተከሰተው ሌላው እጅግ ከባድ የነበረው በአውስትራሊያ የነበረው ሰደድ እሳት ነበር። ይህ ከባድ እሳት 18.6 ሚሊየን ሄክታር (46 ሚሊየን ኤከር፤ 186,000 ስክዌር ኪሎ ሜትር፤ ; 72,000 ስክዌር ማይልስ) ሲሸፍን 5,900 ሕንጻዎችን ጨምሮ 2,779 ቤቶችን አውድሟል። በተጨማሪም የ34 ሰዎች፤ 1 ቢሊየን እንስሳትን ገድሎ ማለፉን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

3ኛ) ከቻይና ሁዋን እንደተቀሰቀሰ የሚነገርለት የኮሮና ቫይረስ COVID-19 ወረርሽኝ እስካሁን ከ7000 ሰዎች በላይ ገድሎ ከ173000 ሰዎች በላይ ይዞ በመላው ዓለም ግስጋሴውን እየጨመረ ዓለማችንን ከባድ ስጋት ላይ ጥሏታል። በዕድሜያችን አይተን በማናቀው መልኩ በረራዎች ቆመዋል፤ ድንበሮች ተዘግተዋል። ትምህርት ቤቶችም እየተዘጉ መላዋ ዓለም በአሁን ሰዓት በጭንቀት ተውጣለች።

4ኛ) ቀጣዩ የዚህ ዓመት የዓለማችን ስጋት የሚቀጥለው ወር ሚያዝያ 21 (April 29) 2012 ዓ.ም የኤቨረስት ተራራን የሚያህል 52768 (1998 IR2) ተብሎ የተጠራ ግዙፍ አስቴሮይድ (ዐለት) ከሰማይ በሰዓት 19,461 እየበረረ ከመሬት በ 3,908,791 ማይልስ ርቀት
ምድርን ማለፉ ነው።

❤️ ቢወድቅ ምድርን ሊጎዳት የሚችለው ይህ አውዳሚ ዐለት ምድርን ስቷት ይሄዳል እንጂ አይነካትምና ተረጋጉ የሚል መልእክቶች ከናሳ እየወጡ ይገኛሉ።

5ኛ) በዚሁ ዓመት እጅግ በዝቶ በምሥራቅ አፍራካ እና በዐረብ ሃገራት ከየመን የተነሣው የአንበጣ መንጋ እህልን በከፍተኛ ሁኔታ አውድሞ ማለፉና ሄደ ሲባል እንደገና እየተፈለፈለ መምጣቱ ከባድ ነው።

❤️ ከሀገራችን ከኢትዮጵያ ጋር ተያይዞ የ2012 ልዩ ክስተት የሚሆነው በጁን 21/2020 (በእኛ በኢትዮጵያ አቈጣጠር ሰኔ 14/2012 ዓ.ም.) ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ መታየቱ ነው፡፡ ክስተቱም ወለጋ አካባቢ ጀምሮ፣ ከፊል ጎጃምን፣ ከፊል ጎንደርን ዐልፎ ወደ ወሎ በተለይ ላሊበላ አካባቢ ድረስ ስለሚታይና ቀኑ የሚጨልምበት ስለሚሆን በሕይወት ዘመናችን ልናየው የምንችለው አስደማሚ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በአንድሮሜዳ መጽሐፍ የጻፍነውን አንብቡ።

❤️ እግዚአብሔር ምድራችንን ከክፉ ነገር ይሰውርልን ዓመቱን በሰላም ያሳልፍልን እያልን አምላክ ቢፈቅድ የሚመለከታቸውን እንግዶችን በመጋበዝ በተከሠቱት እና በሚከሠቱት ክስተቶችን ዙሪያ በአንድሮሜዳ የቴሌቭዥን መርሐ ግብር ላይ በስፋትና በጥልቀት የምንዳስስ ይሆናል።
[መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ መጋቢት 9/ 2012 ዓ.ም]
#Ethiopia #Rodas #EyohaMedia

Видео [በ2012 ዓ.ም ምድራችንን የሚገጥሟት ከባባድ ፈተናዎች] መገቢ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ! канала Eyoha Media
Показать
Комментарии отсутствуют
Введите заголовок:

Введите адрес ссылки:

Введите адрес видео с YouTube:

Зарегистрируйтесь или войдите с
Информация о видео
20 марта 2020 г. 0:33:03
00:11:22
Другие видео канала
"ዕለተ ምጽአት" መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ"ዕለተ ምጽአት" መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰየ2012 የማያውያን የዘመን ቀመር ፍጻሜና ኢትዮጵያ S 2 E 6  ክፍል 1የ2012 የማያውያን የዘመን ቀመር ፍጻሜና ኢትዮጵያ S 2 E 6 ክፍል 1"ፍየል ፋሽን ሆኗል!" ባለ 650 ብሩ ዶሮ እና ባለ 15 ሺህ ብሩ ፍየል! Ethiopia | Eyoha Media | Habesha"ፍየል ፋሽን ሆኗል!" ባለ 650 ብሩ ዶሮ እና ባለ 15 ሺህ ብሩ ፍየል! Ethiopia | Eyoha Media | Habesha"ሀገሬ ምን ነካት!?" አስደናቂ ንግግር በመምህር መስፍን | Ethiopia"ሀገሬ ምን ነካት!?" አስደናቂ ንግግር በመምህር መስፍን | Ethiopiaበመኪና ሰርፕራይዝ ተደረገች!ለጀግና ሚስቴ ለልጄ እናት ያንስብሻል! Ethiopia |  Eyoha Media | Agape Sakበመኪና ሰርፕራይዝ ተደረገች!ለጀግና ሚስቴ ለልጄ እናት ያንስብሻል! Ethiopia | Eyoha Media | Agape Sakሊታይ የሚገባው (ክፍል 1) በ13 ዓመት ታዳጊ የኒውክለር አሠራር ጥበብና 4 መጻሕፍት ደራሲሊታይ የሚገባው (ክፍል 1) በ13 ዓመት ታዳጊ የኒውክለር አሠራር ጥበብና 4 መጻሕፍት ደራሲክፍል 2| "በስደት ያለ ሰው ሁሉ ቅድሚያ ለራሱ መስጠት አለበት!" Ethiopia | Ethiopiaክፍል 2| "በስደት ያለ ሰው ሁሉ ቅድሚያ ለራሱ መስጠት አለበት!" Ethiopia | Ethiopiaየጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር- ግንቦት 15/2012 ዓ/ምየጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር- ግንቦት 15/2012 ዓ/ምሚስትራዊው እና ተዓምረኛው ሰባት /7 ቁጥር ክፍል 2 ANEDEROMEDA JTV ETHIOPIAሚስትራዊው እና ተዓምረኛው ሰባት /7 ቁጥር ክፍል 2 ANEDEROMEDA JTV ETHIOPIAእናት እኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ወርቅ ናት // by Mesfin Solomon በመምህር መስፍን ሰሎሞንAugust 30, 2020እናት እኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ወርቅ ናት // by Mesfin Solomon በመምህር መስፍን ሰሎሞንAugust 30, 2020ዐውደ ስብከት  // እናንተ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁዐውደ ስብከት // እናንተ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁበሀይቅ ህገወጥ ተያዘ፣ጆማ ዞን 1427 ሱቆች ተያዙ፣ዜጎች ወደ ሀገር ገቡ!ጳግሜ 4 ሀሙስ#Best breaking news#በሀይቅ ህገወጥ ተያዘ፣ጆማ ዞን 1427 ሱቆች ተያዙ፣ዜጎች ወደ ሀገር ገቡ!ጳግሜ 4 ሀሙስ#Best breaking news#ስለ ገነት +++ እፀ ሕይወት +++ ስለ እፀዎ ገነት +++ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ +++ Ethiopian Orthodox Tewahdo Sibketስለ ገነት +++ እፀ ሕይወት +++ ስለ እፀዎ ገነት +++ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ +++ Ethiopian Orthodox Tewahdo SibketMemhr D.r Zebene Lema መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ የማንቂያ ደወል በቦሌ መድኃኔዓለምMemhr D.r Zebene Lema መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ የማንቂያ ደወል በቦሌ መድኃኔዓለምበእጅጉ አደገኛ ስለሆነው ቀጣዩ ጎርፍና የሙቀት ወበቅ መረጃበእጅጉ አደገኛ ስለሆነው ቀጣዩ ጎርፍና የሙቀት ወበቅ መረጃዩፎ ኤሊያንስ እነማናቸው መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ megabe hadiss dr rodass tadeseዩፎ ኤሊያንስ እነማናቸው መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ megabe hadiss dr rodass tadeseአስፈሪዋ ድብቋ ሁለተኛዋ ፀሐይ መቼ ትታያለች?አስፈሪዋ ድብቋ ሁለተኛዋ ፀሐይ መቼ ትታያለች?የኢትዮጵያ አስደናቂ ጥንታውያን ጥቅሎች በሰሜን አሜሪካ በዶክተር ሮዳስ ታደሰ S2 E3 ........ክፍል 1የኢትዮጵያ አስደናቂ ጥንታውያን ጥቅሎች በሰሜን አሜሪካ በዶክተር ሮዳስ ታደሰ S2 E3 ........ክፍል 1በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፤Megabe Haddis Rodas Tadese የ2008 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብ፤ የ2008 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብበመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፤Megabe Haddis Rodas Tadese የ2008 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብ፤ የ2008 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብውይይት ከመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ጋር #Megabe_Hadis_Dr_Rodas_Tadesseውይይት ከመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ጋር #Megabe_Hadis_Dr_Rodas_Tadesse
Яндекс.Метрика