Загрузка страницы

ቤተክርስቲያን ላይ ለምን ፈተና ይበዛል? Deacon Henok Haile ሄኖክ ኃይሌ መረቡን ወደ ጥልቁ ጣሉት ሉቃ 5:3 ፥ መረቡን በስተቀኝ ጣሉ ዮሐ 21:6

#ቤተክርስቲያን ላይ ለምን ፈተና ይበዛል ###
---መረቡን ወደ ጥልቁ ጣሉት-- መረቡን በስተቀኝ ጣሉ--
ከመምህር #ሄኖክኃይሌ
ስምዖንና ጓደኞቹ ዓሣ አጥማጆች ናቸው። ሌሊቱን ሙሉ ሲያጠምዱ
አድረው አንድ ዓሣ እንኳን ሳይይዙ ነጋባቸው። ባዶ መረባቸውን ይዘው
እያለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እነርሱ መጣ።
አስተምሮ ከጨረሰ በኋላ ስምዖንን : "ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል
መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ" አለው። ስምዖን ከአምስት ዓመቱ
ጀምሮ ዓሣ ሲያጠምድ ያደገ የሃምሳ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነው።
ሆኖም "ጥርሴን የነቀልኩበት ሙያ ነው" ብሎ ሳይመፃደቅ "አቤቱ
ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም። ነገር ግን በቃልህ
መረቦቹ እጥላለሁ" አለ። የጌታን ትእዛዝ አክብረው ወደ ጥልቁ ፈቀቅ
ብለው መረባቸውን ሲጥሉ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ ፣ መረቦቻቸውም
ተቀደዱ። በሌላ ታንኳ የነበሩት ጓደኞቻቸውን እንዲያግዙአቸው
ጠሩአቸው። ታንኳው እስኪሠጥም ድረስ መረቡ በዓሣ ተሞላ።
ይህንን ተአምር ያዩ ሁሉ ሲደነቁ ስምዖን ጴጥሮስ ግን ጌታችንን ፈራው።
በዚህ ትልቅ ባሕር ውስጥ ያለውን መርምሮ ካወቀ በእኔ ልብ ውስጥ
ያለውን ኃጢአትማ እንዴት ያውቅብኝ ይሆን? ብሎ ተጨነቀ ፣ የረከሰ
ሕይወቱን አስቦ ራሱን ተፀየፈ። ከኢየሱስ ጉልበት ላይ ወድቆ "ጌታ ሆይ
እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ" አለው። ጌታ ግን "አትፍራ ከእንግዲህ
ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ" አለው። ያቺ ዕለት ስምዖን
ጴጥሮስና ጓደኞቹ ጌታ ባዘዛቸው መሠረት መረብ እየጣሉ ዓሣ
ማጥመድ የጀመሩባት ዕለት ሆነች። (ሉቃ 5:3)
ይህ ከተፈፀመ ከሦስት ዓመታት በኋላ ጌታችን በመስቀል ተሰቅሎ ሞቶ
ከተነሣ በኋላ ትንሣኤውን ሙሉ በሙሉ ያላመኑት ስምዖን ጴጥሮስና
ጓደኞቹ ዓሣ ለማጥመድ ወደ ባሕር ሔደው ነበር። ጌታችን በዚህ ጊዜ
ከመካከላቸው ተገኝቶ "አንዳች የሚበላ አላችሁ?" አላቸው። እነርሱም
የለንም አሉት። ይህን ጊዜ "መረቡን በታንኳይቱ በስተቀኝ ጣሉት
ታገኙማላችሁ" አላቸው። መረቡን ሲጥሉ ከዓሣው ብዛት የተነሣ
ሊጎትቱት አቃታቸው። (ዮሐ 21:6)
በጌታ ትእዛዝ ዓሣ ሁለት ጊዜ የሚጠመድባት ይህች መረብ በዓሣ
የተመሰልን እኛን የሰበሰበች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት።
በመጀመሪያው ዙር ዓሣ የማጥመድ ሥራ የተካሔደው "ወደ ጥልቁ
በመሔድ ነበር" ቤተ ክርስቲያን ከዚህች ዓለም ባሕር ውስጥ ብዙዎችን
አጥምዳለች። በዚህ ዓለም በኃጢአት ዐዘቅት ውስጥ ጠልቀው የገቡትን
ሰዎች ሳይቀር መረብዋ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጥልቁ ፈቀቅ ብላ አጥምዳ
ሰብስባለች። በዚህ ነፍሳትን የማጥመድና ወደ መረቡ የማስገባት ሥራ
ላይ የተመደቡት እነቅዱስ ጴጥሮስ ቢሆኑም ከዓሣዎቹ ብዛት የተነሣ
ለብቻቸው ሊወጡት አልቻሉም። ስለዚህ በሌላ ታንኳ የነበሩ
ጓደኞቻቸውን ጠርተው መረቡን በዓሣ ሞሉት። እነዚህ በረዳትነት
የተጠሩት የሐዋርያት ጓደኞች ምእመናንን ከዓለም ጥልቅ ውስጥ
በትምህርት እየሳቡ ወደ መረቧ ቤተ ክርስቲያን ሲያስገቡ የኖሩ አርድእት
፣ ሐዋርያውያን አበው ፣ ሊቃውንትና ካህናት ናቸው። በጴጥሮስና
በመሰሎቹ ትጋት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ዓሣዎች ተሞልታለች።
ዓሣዎቹ በበዙ ጊዜ መረቡ ተቀድዶ ነበር። እንደዚሁም ኃጢአተኛውን
ከጻድቁ ክፉውን ከደጉ ሳትለይ ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበችው ቤተ
ክርስቲያን በየጊዜው በዓሣዎቿ ብዛት ብዙ የመቀደድ ፈተና ገጥሟታል።
አንዳንድ ዓሣዎች ከባሕር ከወጡ በኋላ ወደ ባሕር ለመመለስ ሲታገሉ ፣
አንዳንዶቹ ባሕር ውስጥ እያሉ እንደሚዋኙት ሊዋኙ ሲሞክሩ ፣ አንዳንድ
ዓሣዎች መረብ ውስጥ ገብተው ሲፋለሙ መረቡን ቀድደውት ነበር።
የእኛዋ መረብ ቤተ ክርስቲያንም ይህ ዓይነቱ በዓሣዎቿ ጦስ የመቀደድ
ችግር ሁሌ እንደገጠማት እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች።
ይህ ሁሉ ችግር ግን ጌታችን ዳግም እስኪመጣ ድረስ ነው። ወደነ ቅዱስ
ጴጥሮስ ድጋሚ መጥቶ መረቡን ጣሉ ያለው ጌታ ስለ ቤተ ክርስቲያንም
ይህን ማለቱ አይቀርም። እስቲ ሁለተኛውን የዓሣ ማጥመድ ሥራ
አስተውለን እናንብበው። መጀመሪያ "ወደ ጥልቁ ጣሉ" ያለው ጌታ
ከትንሣኤ በኋላ ግን "በስተቀኝ ጣሉ" ብሏል። ከጥልቁ ብዙ ዓሣዎች
የሰበሰበችው መረብ ቤተ ክርስቲያን ጌታ ዳግም ሲመጣ ድጋሚ ዓሣ
ትሰበስባለች። ያን ጊዜ ግን የምትሰበስበው "በስተቀኝ" ብቻ ነው።
በዓሣዎችዋ ብዛት ስትቀደድ የኖረችው ቤተ ክርስቲያን ከትንሣኤ በኋላ
ግን ዓሣዎችዋ ብዙ ቢሆኑም እንኳን አትቀደድም። ምክንያቱም ጌታ
"በስተቀኝ ጣሉ" እንዳለው ከትንሣኤ በኋላ ወደ መረቡ የሚገቡት ጌታ
አስቀድሞ በቀኙ ያቆማቸው ቅዱሳን ሰማዕታት ምእመናን ናቸው።
ቅዱሳን ደግሞ የቱንም ያህል በቁጥር ቢበዙ መረብዋ እንድትቀደድ
አያደርጉም።
ጌታችን ዳግም መጥቶ መረብዋን ቤተ ክርስቲያን በሚያስጥልበት ጊዜ
በስተቀኝ ሆነው ከሚገቡት ከነቅዱስ እስጢፋኖስ ፣ ከመጥምቁ ዮሐንስ
ጋር ፣ ከሁሉም ቅዱሳን ሰማዕታት ጋር ለመገኘት ያብቃን።
ዲን ሄኖክ ኃይሌ

Видео ቤተክርስቲያን ላይ ለምን ፈተና ይበዛል? Deacon Henok Haile ሄኖክ ኃይሌ መረቡን ወደ ጥልቁ ጣሉት ሉቃ 5:3 ፥ መረቡን በስተቀኝ ጣሉ ዮሐ 21:6 канала ኦርቶዶክስ ዜማ Orthodox Zema
Показать
Комментарии отсутствуют
Введите заголовок:

Введите адрес ссылки:

Введите адрес видео с YouTube:

Зарегистрируйтесь или войдите с
Информация о видео
19 октября 2019 г. 21:15:21
00:19:37
Другие видео канала
Deacon Henok Haile ይህ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።Deacon Henok Haile ይህ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።"መንግስት ያንተ ናትና ኃይል ክብር ምስጋና ለዘላለሙ አሜን" | አባታችን ሆይ | Part 10 | ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ"መንግስት ያንተ ናትና ኃይል ክብር ምስጋና ለዘላለሙ አሜን" | አባታችን ሆይ | Part 10 | ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌመስቀል እና ኢትዮጵያ | ልዩ የበዓል ዝግጅትመስቀል እና ኢትዮጵያ | ልዩ የበዓል ዝግጅትEthiopia Semayat ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌEthiopia Semayat ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌየሰንበት መዋያ እንግዳ:-ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌየሰንበት መዋያ እንግዳ:-ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌመምህር ሄኖክ ኃይሌ | Memeher Henok Haile| Ethiopian Orthodox church Preachingመምህር ሄኖክ ኃይሌ | Memeher Henok Haile| Ethiopian Orthodox church Preachingድንግል ማርያም ለእኛ መዳን ድርሻ አላት? +++ በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ +++ Ethiopian Orthodox Sibket by Diqon Henock Haileድንግል ማርያም ለእኛ መዳን ድርሻ አላት? +++ በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ +++ Ethiopian Orthodox Sibket by Diqon Henock Haileአሁንም ወደፊትም ኦርቶዶክስ ነኝ PROPHET HENOK GIRMA[JPS TV WORLD WIDE] 2020አሁንም ወደፊትም ኦርቶዶክስ ነኝ PROPHET HENOK GIRMA[JPS TV WORLD WIDE] 2020Dn Henok Haile ኃጢአቱን  የሚሰውር እይለማምDn Henok Haile ኃጢአቱን የሚሰውር እይለማም++ወደ ፈጣሪ መመለስ ++ በመ/ር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)#45++ወደ ፈጣሪ መመለስ ++ በመ/ር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)#45"በሰማያት የምትኖር" | አባታችን ሆይ | Part 3 | ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ"በሰማያት የምትኖር" | አባታችን ሆይ | Part 3 | ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌዓለም ሰላሟን አግኝታለች፡፡ ቆይታ ከዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ ጋር | Deacon Henok Haile |ዓለም ሰላሟን አግኝታለች፡፡ ቆይታ ከዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ ጋር | Deacon Henok Haile |Semayat እግዚአብሔር ያስታውሳል ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌSemayat እግዚአብሔር ያስታውሳል ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ" ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።" (የማቴዎስ ወንጌል 5:6) በድያቆን ሄኖክ ሃይለ" ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።" (የማቴዎስ ወንጌል 5:6) በድያቆን ሄኖክ ሃይለውስተ ጽባሕ ነጽሩ(ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ) በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገ/ኪዳን ገብረ ኪዳን ግርማ  Aba Gebre Kidan Gebrekidan Girmaውስተ ጽባሕ ነጽሩ(ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ) በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገ/ኪዳን ገብረ ኪዳን ግርማ Aba Gebre Kidan Gebrekidan Girma"የመስቀሉ ቃል"|   በዲ.ን ሄኖክ ኃይሌ"የመስቀሉ ቃል"| በዲ.ን ሄኖክ ኃይሌየጠገበች ሰውነት የማር ወለላ ትንቃለች የተራበች ሰውነት ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጥማታል: በአባ ገብረ ኪዳን ግርማ Aba Gebre Kidan Gebrekidanየጠገበች ሰውነት የማር ወለላ ትንቃለች የተራበች ሰውነት ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጥማታል: በአባ ገብረ ኪዳን ግርማ Aba Gebre Kidan Gebrekidanቢያደምጡት እጅግ ይጠቀማሉ "የወጣቶች ሕይወት ከጋብቻ በፊት" | ክፍል 1 | በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌቢያደምጡት እጅግ ይጠቀማሉ "የወጣቶች ሕይወት ከጋብቻ በፊት" | ክፍል 1 | በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ"እስከ ቤተልሔም እንሂድ"          በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ"እስከ ቤተልሔም እንሂድ" በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌDn Henok Haile እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ ሰባኬ ወንጌል ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ (zomi)Dn Henok Haile እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ ሰባኬ ወንጌል ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ (zomi)
Яндекс.Метрика