Загрузка страницы

Atronos: Ordinary Heroes, -The Story of Wessenyelesh Debela : Part 1

የአዘቦት ጀግኖች (Ordinary Heroes) ዜጎች ተከታታይ መሳጭ ታሪኮች በአትሮኖስ
እንደምንድናችሁልን የተወደዳችሁ የአትሮኖስ ታዳሚያን፣ በአትሮኖሳችን፣ ያልተነጋገርንባቸውን ጉዳዮች ፊት ለፊት ለማምጣት፣ ችላ ያልናቸውንም አገራዊ የታሪክ፣ የፖለቲካና የማህበረሰብ ጭብጦች ተገቢው ዋጋና ትኩረት እንዲሰጣቸው የምንጥርበት፤ አዲስ ፈለግ የምናስስበት ዝግጅት መኾኑን ለእናንተ መንገር መቼስ ጥቂት ግር ያሰኛል፡፡ በሚገባ ታውቁታላችሁና፡፡ ኾኖም፣ አሁንና ከአሁን በኋላ ለሚቀላቀሉን ታዳሚዎቻችን መጠቆሙ ግን አይከፋም፡፡
የሀገራችንን ትላንት ያለአርትኦት ለማየት እንዲያስችል፤ የኢትዮጲያችንን ሁለንተናዊ ስብጥርና ህብር ለመረዳት እንዲበጅ፤ በአትሮኖስ እጅግ አስደናቂ የዜጎችን እውነተኛ ታሪኮች በተከታታይ ማቅረብ ጀምረናል፡፡ ዛሬም በቀጣይነት የምናቀርበውን ተረክ የመጀመሪያ ክፍል ይዘናል፡፡
የሀገራችን ታሪክ ከትላንት ስህተት ተምረን ዛሬን ለማስተካከልና ነገን ለማሸብረቅ የሚያስችል መኾኑ ቀርቶ፤ ርዕዮተ-አለማዊ ሻሞላ የሚመዘዝበት የውጥንቅጥ ፖለቲካችን የጦርነት አውድማ ኾኖ ይታያል፡፡ እስካሁንም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የየድርጅቶቹ የአመራር አባላት፣ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሊግ ወይም የማህበራት ልሳናት ወዘተ፤ ሌላውን ተጠያቂ እያደረጉ “እውነታችን ታሪካችን” ያሉትን ጽፈዋል፤ ተናግረዋል፡፡ በየሰልፉና ግዳጁ፣ በመሳደዱና እልቂቱ ውስጥ የነበሩት ግለሰቦች ወይም ዜጎች ግን ዛሬም ድረስ በቂ የመናገርያ መድረክ አላገኙም፡፡በመኾኑም፣ ዜጎች፣ ተራ አባላትና ነዋሪዎች በድርጅት ጭምብል ሳይከለሉ፣ ድርጅታችን፣ ተቋማችን፣ መንግስታችን ወዘተ ሳይሉ፣ እራሳቸው በግል የተጓዙትን ጉዞ፣ የዋሉ ያደሩበትን፣ የተካፈሉትን አውደውጊያም ኾነ ጉባኤ፣ ያለፉበትን መከራም ኾነ ደስታ በሚያውቁትና በእራሳቸው እይታ ልክ ብቻ እንዲተርኩ እናደርጋለን፡፡ ይህም ስለታሪካዊ ፍጻሜዎቹ አዲስ ሥዕል መስጠት ከመቻሉም በተጨማሪ፣ እርግጥ በጊዜውና በቦታው የነበረውን ኹኔታ በቅርበትና በተሻለ ጥራት ለማየት ይረዳል ብለን እናምናለን፡፡ በእነኚህ ተከታታይ ዝግጅቶች አስገዳጅ ኾኖ ጥያቄ መጠየቅ ካላስፈለገን በቀር የእኛን ጣልቃ ገብነት ቀንሰን መድረኩን የምንተወው ለባለታሪኮቹ ነው፡፡ እኛም እናንተም የየታሪካቸውን ሀዲድ እየተከተልን ልብ ሰቅዞ የሚይዝ የህይወት መንገዳቸውን አብረናቸው እንጓዛለን፡፡ ደስ እንደምትሰኙም ተስፋ እናደርጋለን፡፡
የዛሬው ባለታሪካችን ወይዘሮ ወሰንየለሽ ደበላ ናት፡፡ ነዋሪነቷ እዚህ በዩናይትድ እስቴትስ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምሮ በየሳምንቱ በተከታታይ ክፍል፣ የቤተሰቧን የኢትዮጲያ መልክ፣ ከሞት ለማምለጥ የተሽሎከሎከችበትን፣ ከአዲስ አበባ እስከ ሰሜን በረሃዎች የተንከራተተችበትን አስደናቂ ታሪክ ከኋላ አንስታ ታስጉዘናለች፡፡
ክቡራትና ክቡራን፣ ወሰንየለሽ ደበላ የምታጋራንን ታሪክ እየተከታተላችሁ ሐሳቦቻችሁን ትሰጡ ዘንድ በክብር ተጋብዛችኋል፡፡ ወይዘሮ ወሰንየለሽ ደበላ የሚያስደምም የህይወት ጉዞዋን በአትሮኖስ በኩል በተከታታይ ታወጋችኋለች፡፡ ይህንን ለማድረግ መልካም ፈቃዷ ስለኾነም እናመሰግናታለን፡
ይህ የርዕዮት አትሮኖስ ነው፡፡ እነሆ የዛሬው፡፡

Видео Atronos: Ordinary Heroes, -The Story of Wessenyelesh Debela : Part 1 канала Reyot
Показать
Комментарии отсутствуют
Введите заголовок:

Введите адрес ссылки:

Введите адрес видео с YouTube:

Зарегистрируйтесь или войдите с
Информация о видео
18 февраля 2021 г. 0:00:17
00:30:33
Другие видео канала
አብይ አህመድ የረሸናቸው ስድስት ህፃናት...።አብይ አህመድ የረሸናቸው ስድስት ህፃናት...።አትሮኖስ ፡የበርሃ አሸዋና የባህር አሳዎች ያለቀሱላቸው ነፍሶች … ተከታታይ ታሪክ ክፍል አስራ ዘጠኝአትሮኖስ ፡የበርሃ አሸዋና የባህር አሳዎች ያለቀሱላቸው ነፍሶች … ተከታታይ ታሪክ ክፍል አስራ ዘጠኝብርትኳን ሚደቅሳ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ |የጠ/ሚ/ሩ ፈገግታ ግብጽን አስቆጣ |አሸማጋዮቹ በመንግስት ተገደሉብርትኳን ሚደቅሳ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ |የጠ/ሚ/ሩ ፈገግታ ግብጽን አስቆጣ |አሸማጋዮቹ በመንግስት ተገደሉReminiscing Mekele. የመቐለ ትዝታ… ዜማ ናፍቖት.Reminiscing Mekele. የመቐለ ትዝታ… ዜማ ናፍቖት."ቤት ላፈረስኩባቸው እንዳታስጠልሉ" መንግሥት"የገንዘብ ዝውውር ከልክለናል" ባንኮችየኢትዮጵውያኑ አስከሬን"ቤት ላፈረስኩባቸው እንዳታስጠልሉ" መንግሥት"የገንዘብ ዝውውር ከልክለናል" ባንኮችየኢትዮጵውያኑ አስከሬንየመቀሌው ስብሰባ አጀንዳዎች...''የለሁበትም'' ሙስጠፋ መሐመድ...ጌታቸው ረዳ ስለ ትግራይ ሠራዊት...የመቀሌው ስብሰባ አጀንዳዎች...''የለሁበትም'' ሙስጠፋ መሐመድ...ጌታቸው ረዳ ስለ ትግራይ ሠራዊት...ሰበር፦ ብልፅግና መቀሌ ሊገባ ነው...ሰበር፦ ብልፅግና መቀሌ ሊገባ ነው...ሞት የተፈረደባቸው ህጻናት|“የልማት ግንባታዎች አይኖሩም” መንግሥት|“ብልጽግና አስቆጥቶናል” አሜሪካሞት የተፈረደባቸው ህጻናት|“የልማት ግንባታዎች አይኖሩም” መንግሥት|“ብልጽግና አስቆጥቶናል” አሜሪካ"ምርጫ ቦርድ ሊያፈርሰን ነው" "ከኢትዮጵያ እንፍለስ" ሰልፈኞች "ታጣቂዎች ዘረፉኝ" መንግሥት"ምርጫ ቦርድ ሊያፈርሰን ነው" "ከኢትዮጵያ እንፍለስ" ሰልፈኞች "ታጣቂዎች ዘረፉኝ" መንግሥትአምባሳደሩን አልቀበልም...ሽመልስ አብዲሳ 19 መስጂድ አፈረሱ...ጳጳሱ ሊባረሩ ነው።አምባሳደሩን አልቀበልም...ሽመልስ አብዲሳ 19 መስጂድ አፈረሱ...ጳጳሱ ሊባረሩ ነው።የብልጽግና ኑዛዜ በትግራዩ ጦርነት...7ሚልዮን ህዝብ በሞት አደጋ...የታገዱት የፓርላማ አባላትየብልጽግና ኑዛዜ በትግራዩ ጦርነት...7ሚልዮን ህዝብ በሞት አደጋ...የታገዱት የፓርላማ አባላትመንግስት የህወሓትን ክስ አቋረጠ...የብልጽግናው ሆቴል በካናዳ...ትጥቅ የሚፈቱት ተዋጊዎች..ጠ/ሚ/ሩና ሰሜን ኮሪያመንግስት የህወሓትን ክስ አቋረጠ...የብልጽግናው ሆቴል በካናዳ...ትጥቅ የሚፈቱት ተዋጊዎች..ጠ/ሚ/ሩና ሰሜን ኮሪያትግሉን የቀየረዉ የትግራዩ ፓርቲ..."ልዩ ኃይሉ አይበተንም" የአማራ ክልል...በብልጽግና ሹመኞች የተገደለዉ ሹመኛትግሉን የቀየረዉ የትግራዩ ፓርቲ..."ልዩ ኃይሉ አይበተንም" የአማራ ክልል...በብልጽግና ሹመኞች የተገደለዉ ሹመኛሽግግሩ የተጋረጠበት አስፈሪ አደጋ… ተጻፈ በጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳኤሽግግሩ የተጋረጠበት አስፈሪ አደጋ… ተጻፈ በጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳኤአትሮኖስ ፡የበርሃ አሸዋና የባህር አሳዎች ያለቀሱላቸው ነፍሶች … ተከታታይ ታሪክ ክፍል አስራ ሁለት.አትሮኖስ ፡የበርሃ አሸዋና የባህር አሳዎች ያለቀሱላቸው ነፍሶች … ተከታታይ ታሪክ ክፍል አስራ ሁለት.የሰቆቃን  ሸለቆ የተሻገሩት  ብእሮች… የአብይ አገዛዝ ያልተሰሙ ጉዶች በጨረፍታየሰቆቃን  ሸለቆ የተሻገሩት  ብእሮች… የአብይ አገዛዝ ያልተሰሙ ጉዶች በጨረፍታ“በመንግስት ላይ ኦፖሬሽን አካሄድኩ” “ለዩኒቨርስቲዎች በጀት አልመድብም” ብልጽግና“ብልጽግና ፋሲሽት ነው” የፓርላማ አባልየሚሸጡት የትግራይ ተወላጆች“በመንግስት ላይ ኦፖሬሽን አካሄድኩ” “ለዩኒቨርስቲዎች በጀት አልመድብም” ብልጽግና“ብልጽግና ፋሲሽት ነው” የፓርላማ አባልየሚሸጡት የትግራይ ተወላጆችበኤርትራ ተጋሩ ታጋቾች...በአማራ የታሰሩ ተጋሩ...ምክር ቤቱ ይቅርታ ጠየቀበኤርትራ ተጋሩ ታጋቾች...በአማራ የታሰሩ ተጋሩ...ምክር ቤቱ ይቅርታ ጠየቀብልጽግናን የወረፉት ፕሬዝደንት… “ሲያሸብሩ ያዝኳቸው” መንግስት… 383 ታሰሩብልጽግናን የወረፉት ፕሬዝደንት… “ሲያሸብሩ ያዝኳቸው” መንግስት… 383 ታሰሩበትግራይ የተገደሉ መምህራን...የአፍሪካ ህብረት የትግራይ መሣሪያ ተረከ...በሥራ አስፈጻሚዎቹ ለቀቁበትግራይ የተገደሉ መምህራን...የአፍሪካ ህብረት የትግራይ መሣሪያ ተረከ...በሥራ አስፈጻሚዎቹ ለቀቁ“ውሃ በተደፋ ቁጥር ስልጣን ልቀቅ አትበሉኝ” አብይ“አገር ስለደፋህ ነው ልቀቅ የምንልህ” ቴዎድሮስ“ውሃ በተደፋ ቁጥር ስልጣን ልቀቅ አትበሉኝ” አብይ“አገር ስለደፋህ ነው ልቀቅ የምንልህ” ቴዎድሮስ
Яндекс.Метрика