Загрузка...

DW Amharic የሚያዝያ 27 ቀን 2017 የዓለም ዜና

• የእስራኤል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገቡ።
• በአማራ ክልል ደሴ እና ወልድያ ከተሞች የአጭር ርቀት አሽከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ።
• የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሱዳን በተፈጸመ የጅምላ ፍጅት ተባባሪ ሆናለች በሚል የሱዳን መንግሥት ያቀረበውን ክስ የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
• ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በምዕራባዊ ኬንያ በምትገኘው ኬሐንቻ የተባለች ከተማ በጫማ ተመቱ።
• ወግ አጥባቂዎቹ የክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት (CDU) እና ክርስቲያን ሶሻል ኅብረት (CSU) ለጀርመን ጥምር መንግሥት የመሠረቱበትን ሥምምነት የመሀል ግራ ርዕዮት ከሚያቀነቅነው ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ (SPD) ጋር ተፈራረሙ። በሥምምነቱ የተመሠረተው ጥምር መንግሥት ነገ ማክሰኞ ቃለ መሐላ ይፈጽማል።
• አማራጭ ለጀርመን (AfD) የተባለው ፓርቲ “ቀኝ አክራሪ” ብሎ በፈረጀው የጀርመን የሀገር ውስጥ የሥለላ መሥሪያ ቤት ላይ ክስ መመሥረቱን አስታወቀ።
• እስራኤል ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመያዝ እና ላልታወቀ ጊዜ የፍልስጤም አካል የሆነውን ሠርጥ ለመቆጣጠር የሚያስችል ዕቅድ ማጽደቋን ሁለት ባለሥልጣናት ተናገሩ።

Видео DW Amharic የሚያዝያ 27 ቀን 2017 የዓለም ዜና канала DW Amharic
Страницу в закладки Мои закладки
Все заметки Новая заметка Страницу в заметки