Загрузка страницы

Tigist Fantahun (ትግስት ፋንታሁን) - Tizita (ትዝታ)

I do not claim any copy right, and just sharing this beautiful Tizita song with fellow fans of Tigist Fantahun's songs ... LYRICS listed below...
ሂድ ብዬ ነበረ ቆርጦልኛል ብዬ
አልቻልኩም ተመለስ ተረታሁ ሸግዬ
ሂድ ሲል አንደበቴ ቆይ ይላል አንጀቴ
አልተስማሙልኝም ዳኝልኝ በሞቴ

ሸሞንሟናዬ ና ቃሌን አትይብኝ
አፌ በደል ሆኖ በሱ አትፍረድብኝ
ዝናብ ያርግህና ፍሰስ ከበላዬ
ባንተ መጠመቁን አይጠላም ገላዬ

አገር ስም ያውጣልኝ ተመለስ ግድ የለም
ብታማ ለወር ነው ባጣህ ለዘላለም
እንደኔ ማን አለ በእንባው ለፍቶ አዳሪ
ለተወደደ ልብ ፍቅር አበዳሪ

አቤት ብዬ ነበር ክሴ የት ደረሰ
በምን ያወርዱታል በፍቅር የነገሰ
ደራሽ ያርግህና ይዘኸኝ ተሻገር
ድረሱልኝ ብሎ አፌም አይናገር

ሸሞንሟናዬ ና ቃሌን አትይብኝ
አፌ በደል ሆኖ በሱ አትፍረድብኝ
ዝናብ ያርግህና ፍሰስ ከበላዬ
ባንተ መጠመቁን አይጠላም ገላዬ

ሂድ ብዬ ነበረ ቆርጦልኛል ብዬ
አልቻልኩም ተመለስ ተረታሁ ሸግዬ
ሂድ ሲል አንደበቴ ቆይ ይላል አንጀቴ
አልተስማሙልኝም ዳኝልኝ በሞቴ

Видео Tigist Fantahun (ትግስት ፋንታሁን) - Tizita (ትዝታ) канала Mazziwa
Показать
Комментарии отсутствуют
Введите заголовок:

Введите адрес ссылки:

Введите адрес видео с YouTube:

Зарегистрируйтесь или войдите с
Информация о видео
17 мая 2012 г. 12:15:43
00:07:30
Яндекс.Метрика