Загрузка страницы

Ethiopian Eclipses የፀሀይ ግርዶሽን መመልከቻ መሳርያ በቤታችን እንዴት መስራት እንችላለን?

ፀሃይ ግርዶሽ የፊታችን እሁድ ሰኔ 14 በኢትዮጵያ፣ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኮንጎ፣ በፓኪስታን እና በህንድ የተወሰኑ ስፍራዎች፣ እንዲሁም በቻይና ይከሰታል። የአየር ሁኔታ የሚፈቅድ ከሆነ በእነዚህ አገራት ያሉ የተወሰኑ ህዝቦች ግሩም የሆነውን የእሳት ቀለበት የሚመስል አስገራሚ የተፈጥሮ ክስተት በሰማይ ላይ ያያሉ። በርካታ አይነት የፀሃይ ግርዶሽ አይነቶች ሲኖሩ፣ በጥቅሉ የፀሃይ ግርዶሽ የሚፈጠረው ጨረቃ በምድርና በፀሃይ መካከል በመግባት የፀሃይ ብርሃን ወደ ምድራችን እንዳይደርስ ስለምትጋርድ ነው።

መሬት ፀሃይን እንዲሁም ጨረቃ መሬትን በelliptical orbit እንደሚሽከረከረሩ ይታወቃል። የእሁዱ የእሳት ቀለበት የሚመስል የፀሃይ የቀለበት ግርዶሽ (Annular Solar Eclipse) የሚከሰተው ፀሃይ ለመሬት ቀረብ ስትል፣ ሙሉ ጨረቃ (Full Moon) ደግሞ ከመሬት ትልቁ ርቀቷ ላይ ስትሆንና እነዚህ የፀሃይ፣ የመሬት እና የጨረቃ የመቀራረብና የመራራቅ ክስተቶች ደግሞ በኦርቢት የመሽከርከር ወቅት ሶስቱም በአንድ ቀጥታ መስመር ውስጥ ተሰልፈው ሲገኙ ነው። በዚህ ቅጽበት ሙሉ ጨረቃ ከምድር ስትርቅ ወይም ወደ ፀሃይ ስትቀርብ ፀሃይን ሙሉ በሙሉ መሸፈን ስለሚያቅታት በጨረቃ የክበብ ዙሪያ የቀለበት ቅርፅ የያዘ የፀሃይ ትርፍ ነጽብራቃዊ አካል ይታያል።

የናሳ ካርታ እንደሚያሳየው፣ በኢትዮጵያ ይህ የቀለበት የፀሃይ ግርዶሽ የሚከሰትባቸውን ቦታዎችን ማየት ይቻላል። በሁለቱ ሰማያዊ መስመሮች ውስጥ ያሉ ቦታዎች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሙሉ የቀለበት የፀሃይ ግርዶሽን (ለምሳሌ ንፋስ መውጫ፣ ላሊበላ እና አካባቢዎቹ) ማየት የሚችሉ ሲሆን፣ እንደ አሶሳ፣ ባህር ዳር፣ አዲስ አበባ እና መቀሌ ያሉ ከተሞች በሌሎችም የኢትጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ደግሞ ከፊላማ የሆነውን የፀሃይ ግርዶሽ ማየት ይችላሉ። እነዚህ ቦታዎች ለምሳሌ የተጠቀሱ ሲሆን ሙሉ መረጃውን በዚህ የናሳ ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል። https://eclipse.gsfc.nasa.gov/…/SEg…/SE2020Jun21Agoogle.html ግርዶሹ የሚታይባቸው ሰዓቶች፡- ነፋስ መውጫ፣ ላሊበላ እና አካባቢዎቻቸው ሙሉ የቀለበት ግርዶሽ የሚታየው በ04:59 UT (Universal Time) ሲሆን (በኢትዮጵያ የሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ 1:59 መሆኑ ነው) ከፊል ግርዶሽ የሚጀምርበት እና የሚጨርስበት ሰዓት በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በመቀሌ በአሶሳ እና በሌሎችም አካባቢዎች በ03:49 UT (Universal Time) አካባቢ ይሆናል (በኢትዮጵያ የሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ 12:49 መሆኑ ነው)። የፀሃይ ግርዶሽን ያለመከላከያ በባዶ አይን መመልከት በፍፁም አይመከርም።

Видео Ethiopian Eclipses የፀሀይ ግርዶሽን መመልከቻ መሳርያ በቤታችን እንዴት መስራት እንችላለን? канала Tesfahun Maru
Показать
Комментарии отсутствуют
Введите заголовок:

Введите адрес ссылки:

Введите адрес видео с YouTube:

Зарегистрируйтесь или войдите с
Информация о видео
19 июня 2020 г. 22:12:53
00:01:50
Яндекс.Метрика